• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 weeks ago
  • 77 Views

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ የጀመረው አዲስ ኩባንያ

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አዲስ አምራች ኩባንያ ተመርቆ ስራ ጀመረ 

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ባቲ ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ የማምረቻ ሼድ ውስጥ ማምረቻ ማሽነሪዎችን በመትከልና በመገጣጠም በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል። 

በምረቃ መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአ/ብ/ክ/መ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሀመድ አሚን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ኩባንያውን በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል። 

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ለኩባንያው አመራሮችና ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ባቲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽኑ አቅም ላላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎች የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም አሁንም አቅም ያላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ያደረገውን ያጠረ የቢሮክራሲ አሰራር እና ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎችን በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት እንዲመጡ ጋብዘዋል።

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቆ ስራ የጀመረው ባቲ ትሬዲንግ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ጥጥን እንደ ግብዓት በመጠቀም ክር የሚያመርት ሲሆን ለምርት ሂደቱ የሚረዳ ከ1.1 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የግብዓት ግዢ ፈፅሟል። 

ኩባንያው አሁን ላይ 300 ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ምርቶቹንም ሙሉ ለሙሉ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪን በማዳን በኩል ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ይጠበቃል። 

Bati Trading PLC inaugurated and start operation in Kombolcha Industrial Park 

Bati Trading manufacturing plc
in Kombolcha Industrial Park was officially inaugurated today. 

H.E Mrs. Fantu Tesfaye, Amhara Regional state Speaker of the Council of Ministers, Aklilu Tadesse, IPDC CEO, Mohammad Amin, mayor of Kombolcha City, and other Federal and Regional officials inaugurated the company officially.

Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse, who spoke at the inauguration ceremony, after sending a congratulatory message to the management and employees of the company, said that 
Bati Trading is a demonstration of the attention given by the Corporation for potential local investors.

Mr. Aklilu also invited local manufacturing companies and investors who still have the potential to come and invest by benefiting from zero waiting time bureaucracy and various incentives implemented by the corporation.

Bati Trading with an investment capital of more than 350 million birr is a cotton yarn manufacturer, which was inaugurated today at Kombolcha Industrial Park, has already purchased 1.1 million dollars worth of raw materials to help with the production process. 

Bati Trading has created job opportunities for about 300 citizens and it is expected to play a major role in saving foreign currency by providing import substituting products to the local market.

#invest_in_zero_waiting_time_bureaucracy