• Striving for eco industrial park
logo

ማስታወቂያ

ማስታወቂያ 
ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፤  

ጉዳዩ፡- የማምረቻ ቦታ ይመለከታል፤
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ከትላልቅ አምራች ኩባንያዎች የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር ለማስተሳሰር፣ ፈጠራን ለማሳደግ፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እንዲቻል በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የማምረቻ ቦታ ለመውሰድ እንዲያመለክቱ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥሪ ያደርጋል። 

የመመልመያ መስፈርት፡- 
አመልካቾች የማምረቻ ቦታ ማግኘት እንዲችሉ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስታርአፕ/ኢንተርፕራይዝ መመሪያ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ከሚመለከተው የፌዴራል፣ የክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ተቆጣጣሪ አካል እውቅና ያለው፣
2. በአግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ፋርማሲዩቲካልስ፣ ማሽነሪ፣ የሕክምና መሳሪያዎች ወይም ሌሎች ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች ለኤክስፖርት ወይም ተኪ ምርትን የሚያመርት፣
3. ከአገር ውስጥ አምራቾች ግብዓቶችን በመጠቀም፣ ጠንካራ የአገር ውስጥ አቅርቦት ሰንሰለት ትስስር መፍጠር የሚችል፣
4. ለአንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ በሥራ ላይ የቆየ እና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
5. ዝርዝር የአዋጭነት ጥናት (የንግድ እቅድ)፣ የምርት ሞዴልና ስያሜ ማቅረብ እና ለታቀደው ዘርፍ አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅም ማሳየት የሚችል፣
6. ኮርፖሬሽኑ ለሥራ ቦታው ያወጣቸውን መመዘኛዎች ስታንዳርዶች ማክበርና መተግበር፣
7. በንግድ ሕግ እንደ ግል ድርጅት ወይም የአክሲዮን ኩባንያ የተመዘገበ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው እና ግብር ከፋይ መሆን አለበት እና
8. የሥራ ዕድል መፍጠር እና የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማመቻቸት የሚችል፡፡

ማበረታቻዎች እና ጥቅማ ጥቅሞች፡- 
የተመለመሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ ማበረታቻዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ በኮርፖሬሽኑ በኩል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1. በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ መሰረተ ልማቱ የተሟላ የለማ መሬት ማግኘት።
2. የአራት ዓመት የመሬት ሊዝ ክፍያ የእፎይታ ጊዜ።
3. የገበያ ትስስር መፍጠር እና ወደ ትላልቅ የማኑፋክቸሪንግ ደረጃዎች የማሸጋገር ድጋፍ።
በመሆኑም ፍላጎት ያላቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አጠቃላይ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸውን እንዲያዘጋጁ እና ከዚህ ልዩ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይበረታታሉ።
የማመልከቻ ቦታ፡- 
1. አመልካቾች የፕሮጀክት ፕሮፖዛል እና ደጋፊ ሰነዶችን ቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ በሚገኘው  የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት በአካል ተገኝተው ማስገባት አለባቸው።

#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone 
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein 
#exportprocessingzone 
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia 
#HawassaSEZ 
#TextileHub 
#PlugAndPlay 
#AfricaRising 
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady 
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#HawassaSEZ 
#InvestEthiopia
#itparks 
#information 
#informationtechnology 
#innovation 
#InnovationInAction
#russia
#russiaembassyinaddisababa
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30