• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 weeks ago
  • 52 Views

የሁለቱ ተቋማት የልምድ ልውውጥ

ገዳ ልዩ ኢኮኖሚ  ዞን ከኮርፖሬሽኑ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ 

የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለስልጣን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የልምድ ልውውጥ አካሂዷል ። 

የልምድ ልውውጡ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች አተገባበርና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን  የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ሞቱማ ተመስገንና ሌሎችም የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት  ተካሂዷል። 

የልምድ ልውውጡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን በማልማትና በማስተዳደር ባለፉት ዓመታት ያካበተውን እውቀትና ሰፊ ልምድ በመጠቀም በቀጣይ 40 ዓመታት በተለያዩ ምዕራፎች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የገዳ ልዩ  ኢኮኖሚ ዞን ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 10 ዓመታት ያካበተው የኢንዱስትሪያላይዜሽን ባህል ፤ እውቀትና ልምድ ለገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ተግባራዊነት ፅኑ መሰረት የሚጥል መሆኑን ጠቁመው ከወዲሁ በቅንጅት መከወን የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። 

ከውይይቱም በተጨማሪ የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን አመራሮች የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።

ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በቀጣይ 4 አስርት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 3ሺ 1 መቶ 50 ሄክታር መሬት ላይ አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለማከናወንና ለሀገር በቀል እንዲሁም ለአለም አቀፍ አልሚዎች ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

ከልምድ ልውውጡ የውይይት መድረክ በተጨማሪም የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ አመራሮች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና በመገኘት አጠቃላይ የመስክ ምልከታም አድርገዋል፡፡