• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 months, 2 weeks ago
  • 175 Views

የቻይና ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካውንስል በኢትዮጵያ

"የቻይና ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካውንስል ለኢትዮጵያ ቴክስታይል ኢንዱስትሪ እድገት ሚናው ከፍተኛ ነው" 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የቻይና ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካውንስል ለኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ እድገት ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ ገለፁ። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት በዛሬው እለት በሸራተን ሆቴል ከቻይና ጨርቃጨርቅና አልባሳት ካውንስል ልዑክ ቡድን ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው። 

በውይይቱም የኮርፖሬሽኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀና አርአያስላሴ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። 

በመድረኩ አቶ አክሊሉ እንደገለፁት የቴክስታይል ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ፤ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ የምርት እድገት ድጋፍ የሚያደርግና ለበርካታ ዜጎቻችን ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው በዚህም ዘርፉን በእጅጉ ለማሳደግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከምንግዜውም በላቀ ጥራትና ፍጥነት እየሰራ መሆኑን አሳውቀዋል። 

መንግስት ዘርፉን ለማበረታታት እና ለማሳደግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሚያመርቱ ኩባንያዎች ከታክስ፤ ከኤክስፖርት እና ከግብር እፎይታ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ማበረታቻዎችን ማዘጋጀቱን የገለፁት አቶ አክሊሉ ኮርፖሬሽኑ ከቻይና ጋር ያለውን የኢንቨስትመንት ትስስር ከቴክስታይልና አፓራልም በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎች ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። 

'The China National Textile and Apparel Council is the backbone of Ethiopia's textile industry development' - Aklilu Tadesse 

Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse, said that the China National Textile and Apparel Council is the backbone of the development of Ethiopia's textile and garment industry. 

The CEO stated this in a discussion with a delegation of the China National Textile and Apparel Council at Sheraton Hotel today. 

In the discussion, including the IPDC CEO Aklilu Tadesse, Commissioner of Ethiopian Investment Commission Hana Arayaselasselie and other senior officials were present 

According to Mr. Aklilu Speech in the forum, he stated that the textile industry has a significant contribution to the Ethiopian economy. He additionally Emphasized that it supports the development of the entire GDP and has created permanent and temporary job opportunities for hundred thousands of our citizens. 

He strongly informed that Industrial Parks Development Corporation is working with higher effective quality and speed than ever before. 

In addition, the government will encourage and develop the sector by taxing companies that produce in industrial parks. Mr. Aklilu, who stated that he has prepared huge incentives in connection with export and tax relief, confirmed that the corporation is ready to increase its investment ties with China in other sectors besides textiles and apparel. 

Mr. Aklilu stated that his government is highly supporting the sector with  huge incentive packages related with export and tax exemptions and he confirmed that IPDC is eager to increase its investment ties with China in other sectors besides textiles and apparel.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy