• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 weeks, 5 days ago
  • 112 Views

የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ

"በኢንዱስትሪ ፓርኮች አዳዲስ ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ  ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እንሰራለን" - ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን አዳዲስ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በትብብር  እንደሚሰሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር ) ገለጹ፡፡ 

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጋር በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ያለመ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ 

ዶክተር ፍሰሃ በውይይቱ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመትን ለመሳብ ፤ ገበያ ለማፈላለግ ፤ በፋርማሲዩቲካል ፤ በሀይቴክ ፤ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ፤ በአግሮ ፕሮሰሲግ እና ተያያዥ ኢንቨስትመንቶች ላይ ከፍተኛ ልምድና አቅም ያላቸው  አዳዲስ የዉጭ ኢንቨስተሮች በፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በመላው አለም የሚገኙ ቆንፅላዎች ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን አንስተው ለዚህም ኮርፖሬሽኑ ከምንጊዜውም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በአሰራርና አደረጃጀት ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው በሀገራችን ተግባራዊ የተደረጉ ዘርፈ ብዙ የማክሮ ኢኮኖሚ የሪፎርም ማሻሻያዎች ኢትዮጵያን ለውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸው በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ መሰረተ ልማቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ አጋጣሚ በመሆናቸው አሟጥጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል። 

አያይዘውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንን ጨምሮ ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት የተለያዩ አለምአቀፍ ባዛርና አዉደርዮችን በማዘጋጀት በዘርፉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ይበልጥ አሟጥጦ ለመጠቀም በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ብለዋል። 

"We will work together with Ministry of Foreign Affairs to attract new Foreign Direct Imvestments ( FDI ) in the industrial parks" Fisseha Yitagesu (Dr.) 

Industrial Parks Development Corporation (IPDC) CEO Fisseha Yitagesu (Dr.), announced that the corporation will work closely with Ministry of Foreign Affairs to attract new Foreign Direct Investments (FDI) into Ethiopia's industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone. 

The CEO stated this during a discussion with Ambassador Misganu Arga, the state minister of Ministry of Foreign Affairs Ethiopia, aimed at increasing the flow of foreign investment in Industrial Parks and Dire Dawa Free Trade Zone. 

During a discussion with Ambassador Misganu Arga, the State Minister of the Ministry of Foreign Affairs, IPDC CEO Dr. Fisseha stated that the two entities will cooperate on various aspects to increase the flow of Foreign Direct Investments, especially in pharmaceuticals,  technology, garments and textile and agro processing sectors. 

Ambassador Misganu, on his part, acknowledged that the government's economic reforms will greatly contribute to attract FDI. He additionally stressed the importance of collaboration with stakeholders to fully utilize the investment opportunities within the industrial parks. 

In addition, he said that the ministry should work in cooperation with other stakeholders including Industrial Parks Development Corporation to organize various international investment related bazaars to take full advantage of the good opportunities in the sector.