• Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 hours, 24 minutes ago
  • 7 Views

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር  የአንድ መስኮት ማዕከል አገልግሎት ስራ  ጀመረ

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር  የአንድ መስኮት ማዕከል አገልግሎት ስራ  ጀመረ

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር  የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከሉን በዛሬው እለት አስጀምሯል።

 የአንድ መስኮት ማዕከሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) አስጀምረዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የአክሲዮን ማህበሩ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከል መጀመሩ በልዩ ዞኑ የሚገኙ ባለሀብቶችን የወጪና ገቢ ንግድን  ለማሳለጥና የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት በኩል ትልቅ ሚና ያለው መሆኑንና ቅርንጫፉ በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራ እንዲገባ በመደረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር)  በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ወደ ጅቡቲ ወደብ ለማድረስ የሚያስችል የአንድ መስኮት አገልግሎት መጀመሩን ገልፀው በቀጣይም በሌሎችም ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ይጀመራል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ አምራቾች የሚያመርቷቸውን ምርቶችና ጥሬ እቃን በተቀላጠፈ ሁኔታ  በኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የትራንስፓርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል  የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ መካሄዱ ይታወሳል።
Ethio-Djibouti Railway Launches One-Stop Service at Bole Lemi SEZ

The Ethio-Djibouti Railway Share Company has officially launched its One-Stop Service (OSS) at Bole Lemi Special Economic Zone (SEZ).

The launch event was attended by Dr. Feseha Yetagesu, CEO of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC), and Takele Uma, CEO of Ethio-Djibouti Railway.

Dr. Feseha remarked that the introduction of the railway company OSS service at Bole Lemi SEZ will significantly enhance the logistical capabilities available to investors, thereby boosting Ethiopia’s global competitiveness in the import-export value chain.

Takele Uma emphasized that the new OSS service will enable investors to efficiently transport their products to the Port of Djibouti and import raw materials with greater ease. He added that similar shipping liner OSS services will be expanded to other special economic zones.

It is worth recalling that the IPDC and Ethio-Djibouti Railway recently held discussions aimed at resolving the logistical challenges faced by investors operating within IPDC-administered SEZs and industrial parks.


#IPDC 
#KilintoSEZ 
#NewBeginnings
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark 
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone 
#InvestInEthiopia  
#SEZ  
#BusinessGrowth  
#jobcreation
#railway
#EDR 
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30