• Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 22 hours, 15 minutes ago
  • 27 Views

ፕሮጀክት አገልግሎቱ ለአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሰራውን ጥናት አስረከበ

ፕሮጀክት አገልግሎቱ ለአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሰራውን ጥናት አስረከበ

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) የሰራውን የአዋጭነት ጥናት ሰነድ አጠናቆ አስረክቧል።

የጥናት ሰነዱን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ለአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ አስረክበዋል።

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ፕሮጀክት አገልግሎቱ በሃገራችን ልማትና እድገት ውስጥ የራሱን አሻራ ሲያሳርፍ የኖረ ድርጅት መሆኑን ገልጸው ለአህሪ ሰርተው ያስረከቡት ካሳቫን ወደ ስታርች ምርትነት ለመቀየር የሚያስችል የአዋጭነት ጥናት ሰነድም በኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የሃገሪቱን የጤና ዘርፍ እንዲሻሻል የራሱን ድርሻ መወጣት ችሏል ብለዋል፡፡

የአርማወር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ በፕሮጀክት አገልግሎቱ የተሰራው የጥናት ሰነድ ለምርምር ኢንስቲትዩቱ ከተሠጡት ኃለፊነቶች መካከል አንዱ የሆነውን የሃገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪን ምርታማነት እና ተወዳዳሪነት ማሳደግ መሆኑን ገልጸው ጥናቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀው በማስረከባቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በጥናት ሰነድ ርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬ ህይወት አበበ በበኩላቸው መንግስት የሃገር ውስጥ ምርት አቅርቦትን ለማሻሻልና ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸው በሀገራችን በስፋት የሚመረተውን ካሳቫ ወደ ስታርች ለመቀየር የተሰራው ጥናትም ወደ ትግበራ እንዲገባ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡


በእለቱ ከርክክቡ በተጨማሪ የአዋጭነት ጥናት ሰነዱን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡


የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በሃገራችን የሚገኙ ትልልቅ ተቋማትን የአዋጭነት ጥናት በመስራት ወደ ትርፋማነት ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ያለ ተጠሪነቱ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሆነ አንጋፋ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

#ips
#consulting
#consultingservices
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30