የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከአራት ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተገለጸ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ከአራት ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኮርፖሬሽኑ የገቢ አፈጻጸም ከእቅድ አንጻር ሲታይ አፈጻጸሙ 99 በመቶ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ማደጉን ጨምረው አብራርተዋል፡፡
ከውጪ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በተደረገ የተኪ ምርት እንቅስቃሴ በበጀት ዓመቱ 18 ቢሊየን ብር የሚገመት ምርት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 11 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መመረታቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው ለሚዲያዎች በሰጡት ገለጻ አመላክተዋል፡፡ ይህም ከእቅድ አንጻር ሲታይ አፈጻጸሙ ከመቶ ፐርሰንት በላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ስድስት ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር በበጀት ዓመቱ ለመፍጠር ታስቦ 14 ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር መፈጠሩን የጠቆሙት ዋና ስራ አስጻሚው አፈጻጸሙ 200 ፐርሰንት በላይ መሆኑን አውስተዋል፡፡ ለአፈጻጸም ከእቅድ በላይ ማደግ የውጪ ምንዛሬ ማስተካከያው የራሱ የሆነ አስዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና አላማዎች አንዱ ለዜጎች ስራ እድል መፍጠር መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር ፍሰሃ ተቋሙ በበጀት አመቱ ከ48 ሺ 900 በላይ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመው ይህም ከእቀድ አንጻር ሲታይ የ91 በመቶ አፈጻጸም ማሳየቱን አመላክተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ አንድ ቢሊየን ብር የሚገመት ኢንቨስትመንትን የታሰበ ሲሆን እቅዱን 100 ፐርሰንት ማሳካት ተችሏል፡፡ በበጀት አመቱ ከላይ የተጠቀሰውን ኢንቨስትመንት ወደ ስራ ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር እጅ እና ጓንት ሆነን በመስራት ከ80 በላይ ኩባኒያዎች ኮርፖሬሽኑ ወደ ሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ኢንዲገቡ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች ወደ ውጪ ከሚልኩት ምርቶ በበጀት ዓመቱ 146 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማስገባት ታቅዶ 124 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተጠቁሟል፡፡ ይህም የእቅዱን 85 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
የኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተመሰረተ 10 አመታት ያስቆጠረ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን 11 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ያስተዳድራል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ206 ባለሀብቶች በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን 88ቱ ስራ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ቀሪዎቹ 118 ኩባኒያዎች ደግሞ በተለያየ የግንባታ ስራ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኩባኒያዎች በአጠቃላይ ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡ የባለሀብቶቹን ስብጥር ስንመለከት 38 በመቶ የሚሆኑት ኩባኒያዎች በውጪ ሀገር ዜጎች የተመሰረቱ ሲሆን 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በሀገር ውስጥ ባላሀብቶች የተመሰረቱ ኩባኒያዎች ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 8 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በኢትዮጵያውያን እና በሌላ ሀገር ዜጎች በሽርክና የተቋቋሙ ኩባኒያዎች ናቸው፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#agroprocessing
#jimmaspecialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30