#በመትከል_ማንሰራራት
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች እና ሰራተኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛሉ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 10 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና 2 ኢንዱስትሪ ፓርኮች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ ለማኖር በሀገር ደረጃ የተያዘውን መርሃ ግብር እውን ለማድረግ ችግኞች በመተከል ላይ ይገኛሉ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር)፤የማኔጅመንት አባላትና የስራ መሪዎች በጅማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩ ሲሆን በኮርፖሬስኑ ዋና መስሪያ ቤት እና አዲስ አበባ የሚገኙ ቅርጫፍ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸው ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን አኑረዋል፡፡
በክልል ከተሞች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ቅርጫፍ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ደግሞ በያሉበት አካባቢ አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ላይ ይገኛሉ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአንድ ነጥብ ሶሰት ሚሊየን በላይ ችግኞችን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚተከሉ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ መገለጹ ይታወሳል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 10 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን አፍልቶ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሚገኙበት ለክልሎች እና ከተማ አስዳደሮች በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
በዘንድሮው ሰባተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከስምንት ቢሊየን በላይ ችግኞች ለመተከል ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዛሬ እየተካሄደ ያለው በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከሉ መርሃ ግብር ይህንኑ ሀገራዊ ትልም አፈጻጸም ለማላቅ የሚደረግ መርሃ ግብር ነው፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድሰት አመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 40 ቢሊየን ችግኞችን መትከል መቻሉ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በዓለም ላይ ካሉ ሶስት ዋና ዋና አካባቢን መልሶ እንዲያገግም ከሚያደርጉ መርሃ ግብሮች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#agroprocessing
#jimmaspecialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30