የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር በድሬዳዋ አስጀመረ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ አመራሮች የኮርፖሬሽኑ 2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር በድሬዳዋ አስጀመረዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈሚው ኮርፖሬሽኑ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባስጀመረው የክረምት በጎ አገልግሎት ተግባር የሁለት አቅመ ደካችን ቤት በዘመናዊ መልኩ ገንብቶ በአጭር ጊዜ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ሲሰራ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ በድሬዳዋ የተደረገውም ይህ ንኑ መልካም ተግባር የማስቀጠል ሂደት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዛሬው እለት የተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ና ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ ድጋፎችና መርሃ ግብሮች የሚቀጥል ይሆናል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቀጣይ አምስት አመታት በሚተገብረው ስትራቴጅክ እቅዱ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በየ አመቱ ከሚያገኘው ትርፍ ውስጥ ሁለት ፐርሰቱን የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ አቅዶ በመስራት ላይ ይገኛል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተቀናጁ መሰረተ ልማቶችን በማዘጋጀት ለባለሀብቶች የሚያቀርብ ተቋም እንደ መሆኑ ስራውን በሚሰራባቸው አካባቢዎች ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ማህበራዊ መሰረተ ልማቶችን ሰርቶ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡
የኮርፖሬሽኑ አመራሮች የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብሮችን ከማስጀመራቸው በተጨማሪ አረንጓዴ አሻራቸውን በድሬ ዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና አኑረዋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#weekend
#specialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30