• Striving for eco industrial park
logo

የዚምባብዌ የገንዘብ፤የኢኮኖሚ ልማት እና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን አባላት የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኙ

የዚምባብዌ የገንዘብ፤የኢኮኖሚ ልማት እና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን አባላት የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኙ

ለልምድ ልውውጥ ተልዕኮ ኢትዮጵያ የሚገኙት የዚምባብዌ የገንዘብ፤ የኢኮኖሚ ልማት እና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን አባላት የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎብኝተዋል፡፡


የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ በቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያሉ የመሰረተ ልማት፤የአሰራር፤ እንዲሁም የባለሃብቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱም በሃገራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን አስተዳደር ለማዘመን የሚረዳ ልምድ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ያነጋገሩት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይና የኮርፖሬት ህግ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አዱኛ በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገነቡ መሆናቸውን እና በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ዓለም አቀፍ እውቅናና ዝና ያላቸው ትልልቅ ኩባንያዎች ገብተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

የልኡካን ቡድኑ አባላት የተለያዩ ተቋማትን በዚህ ሳምንት እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

A delegation from Zimbabwe’s Ministry of Finance, Economic Development, and Investment Promotion visits Bole Lemi, Kilinto Special Economic Zones

As part of a knowledge and experience-sharing mission, members of the high-level delegation from Zimbabwe’s Ministry of Finance, Economic Development, and Investment Promotion, who are currently in Ethiopia, visited the Bole Lemi and Kilinto Special Economic Zones.

During the visit, the delegation observed the foundational infrastructure, operational systems, and business activities of investors within the Bole Lemi and Kilinto Special Economic Zones. The delegates emphasized that the experience gained from the visit will support efforts to modernize the management of special economic zones in their own country.

The delegation was welcomed and briefed by Mr. Tariku Adugna, a representative of the Chief Executive Office and Head of Corporate Legal Affairs at the Industrial Parks Development Corporation (IPDC). He explained that the special economic zones under the Corporation are built to international standards and are currently hosting several globally recognized and reputable companies.

The Zimbabwean delegation is also expected to visit other relevant institutions throughout the week.

#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#weekend
#specialeconomiczone

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30