የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር በኮምቦልቻ ከተማ አስጀመሩ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ አመራሮች የኮርፖሬሽኑ የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር በኮምቦልቻ ከተማ የሁለት አቅመ ደካሞችን ቤት እድሳትን አስጀምረዋል ፡፡
ዋና ስራ አስፈሚው ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ባለፉት ቀናት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ማስጀመሩን ገልፀው በኮምቦልቻም የሁለት አቅመ ደካሞችን ቤት በዘመናዊ መልኩ ገንብቶ በአጭር ጊዜ የሚያስረክብ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች አቅም ለሌላቸውና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሱት ዶ/ር ፍሰሃ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ 60 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ድጋፎችን በአይነትና በቁሳቁስ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
በኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት በተጨማሪ ለ 130 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍም ተደርጓል::
የኮርፖሬሽኑ አመራሮች የክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብሮችን ከማስጀመራቸው በተጨማሪ አረንጓዴ አሻራቸውን በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ አኑረዋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#kombolchaspecialeconomiczone
#specialeconomiczone
#corporatesocialresponsibility
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30