• Striving for eco industrial park
logo

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚገኙ ባለሃብቶች የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈሚው በጉብኝታቸው በልዩ የኢኮኖሚ  ዞኑ በስራ ላይ የሚገኙ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎችን  የምርት ሂደትና የስራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን ከባለሃብቶቹ ጋርም በስራ ሂደቱና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴያቸው  ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ባለሃብቶች በስራ እድል ፈጠራ፤በውጭ ምንዛሬ፤በእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር እንዲሁም ተኪ ምርት በማምረት ሂደት ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ዶ/ር ፍሰሃ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮርፖሬሽኑ ስራቸውን በቅርበት እንደሚደግፍ ጠቁመው ኮባንያዎቹም እየሰሩ ያለውን ስራ እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡ 

በኮምቦልቻ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከ6 በላይ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ገብተው በመስራት ላይ ሲሆኑ ከ5000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም ቋሚ የሆነ የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡

#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#kombolchaspecialeconomiczone
#specialeconomiczone
#corporatesocialresponsibility

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30