ለጃፓን ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጭ በተመለከተ ገለጻ ተደረገ
በቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከስብሰባበው ጎን ለጎን ለጃፓን ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጭ በተመለከተ ገለጻ አድርጓል፡፡
የውይይት መድረኩን በጃፓን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የጃፓን ውጪ ንግድ ድርጅት (ጀትሮ) በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን የኢፌዴሪ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክት አስተላልፈዋል፡፡
በጃፓን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ በበኩላቸው በውይይቱ የተሳተፉትን የጃፓን ባለሀብቶች ለነበራቸው ተሳትፎ አመስግነዋል፡፡ የጃፓን ውጪ ንግድ ድርጅት (ጀትሮ) ውይይቱ እውን እንዲሆን ላደረገው አስዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ወስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በተመለከተ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አማካሪ አቶ አለማየሁ ሰይፉ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከባለሀብቶቹ ለተነሱ ጥያቄዎች የልኡካን ቡድኑ አባላት ማብራሪያ ሰተዋል፡፡
በቶክዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፈውን የኢትዮጵያ ልዑክ የመሩት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እውቀታቸውን እና ሀብታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ወስነው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብተዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላ የልኡካን ቡድኑ አባላት በጃፓን ዋና ከተማ ቶክዮ የሚገኘውን የቶዮ ሶላር ዋና መስሪያ ቤት ጎብኝተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ወስጥ ቶዮ ሶላር እና ቶፓን ግራቪቲ የተሰኙ ሁለት ግዙፍ የጃፓን ኩባኒያዎቸ ስራ ላይ ይገኛሉ፡፡
የቶክዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ላለፉት ሶስት አስርተ አመታት በላይ በአፍሪካ ልማት፣ ደህንንት፣ሰላም እና ዓለም አቀፍ አጋርነት ዙረያ የሚመክር ኮንፈረንስ ሲሆን ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው የተዘጋጀው፡፡ ኮንፈረንሱን ከጃፓን መንግስት በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት፣ የተባበሩት መንግስት የልማት ድርጅት እና ዓለም ባንክ በአጋርነት እንደሚያዘጋጁት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#GoldenOpportunity
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#KilintoSEZ
#InvestEthiopia
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#agroprocessing
#kilintospecialeconomiczone
#japaninvestment
#TICAD9
#toyoSolar
#topangravity
#JETRO
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30