የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ትርፋማ መሆን መጀመሩ አበረታች ነው - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)
በ2017 በጀት ዓመት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኪሳራ ወጥቶ ትርፋማ መሆን መቻሉ አበረታች መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህንን የገለጹት የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ከሁለቱ ተቋማት አመራሮች ጋር በመሆን በገመገሙበት ወቅት ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች የድሬ ዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠናን በበጀት ዓመቱ በሙሉ አቅሙ ስራ እንዲጀምር ላደረጉት አስተዋጽኦም ዶ/ር ብሩክ እውቅና ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በስራ እድል ፈጠራ፣ በውጪ ምንዛሬ ግኝት፣ በተኪ ምርት እና የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ለሀገር ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ መልካም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ኮርፖሬሽኑ ከተመሰረት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አስር አመታት ትርፍ ያስመዘገበው ሁለት ጊዜ ብቻ መሆኑን አብራርተው ኮርፖሬሽኑ ባለፈው በጀት ዓመት ከኪሳራ ከመውጣቱ በተጨማሪ ገቢው ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በሁለት እጥፍ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ከአራት ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ያብራሩት ዶ/ር ፍሰሃ ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት እንዲተኩ በተደረገ ጥረት በበጀት ዓመቱ 18 ቢሊየን ብር የሚገመት ምርት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 11 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መመረቱን ጠቁመዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 14 ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር መፈጠሩን ያብራሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው በበጀት አመቱ ከ48 ሺ 900 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን አመላክተዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ አንድ ቢሊየን ዶላር የሚገመት ኢንቨስትመንትን ኮርፖሬሽኑ ወደሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች መሳብ መቻሉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች በበጀት ዓመቱ 124 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጨምሮ ከ40 በላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በባለቤትነት የሚያስተዳደር ግዙፍ ሀገራዊ ተቋም እና በአፍሪካ ቀዳሚ ሀገራዊ ሀብትን የሚያስተዳድር ተቋም ሲሆን በዓለም ላይ 34 ደረጃን እንደያዘ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የሚያስተዳድረው ሀገራዊ ሀብትም 45 ቢሊየን ዶላር ገደማ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#KilintoSEZ
#InvestEthiopia
#EIH
#ethiopianinvestmentholding
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30