ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን ጸጥታና ደህንነት ለማጠናከር የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን አቅም ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን አቅም የማጎልበት ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጸጥታና ደህንነት መምሪያ በ11 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና 2 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሚሰሩ የጸጥታና ደህንነት መምሪያ ቡድን መሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሰጠት በጀመረበት ወቅት ነው፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት በኮርፖሬሽኑ የኦፐሬሽንና ማኔጅመንት ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም የሰላምና ጸጥታ ስራ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አቶ ካሚል ኢንቨስትመንት በተሳካ ሁኔታ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሰላምና ደህንነት ስራ ማጠናከር እንደሚፈልግ ጠቁመው በዚህ ረገድ እተሰጠ ያለው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው የተገኙ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ያመላከቱት ስራ አስፈጻሚው ጥሩ ለሚሰሩ የኮርፖሬሽኑ ባልደረቦች እና ባለድርሻ አካላት እውቅናና የልምድ ልውውጥ የሚሰጥበት ስርዓት መዘርጋት አሰፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙ ደግሞ ችግሮችን በትብብርና በጋራ በመቅረፍ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና በፓርኮች አካባቢ ያለውን የሰላምና ጸጥታ ስራን አስተማማኝ ማድርግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
በኢፌዴሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተቋማትና መሰረተ ልማት ደህንነት አስተባባሪ ረዳት ኮሚሽነር ሰለሞን ከበደ በበኩላቸው ስልጠናው በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚሰሩ የሰላምና ደህንነት ስራዎችን በቅንጅትና በጋራ በመስራት አስተማማኝ የስራ እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያግዝና በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሙያዎችን የእርስ በእርስ ትውውቅና አብሮነት ያጠናክራል ብለዋል፡፡
ለ3 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሰላምና ደህንነት መምሪያ የስራ ድርሻ፤ደንበኛ አያያዝና አገልገሎት አሰጣጥ፤ተቋማዊ እሴትና እምነት ግንባታ፤የተቋማዊ የስራ ባህል ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#mekelespecialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30