በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ከ10 በላይ ባለሃብቶች ስራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን የግንባታ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛሉ
በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በፋርማሲዩቲካል የኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚሰማሩ ከ10 በላይ ባለሃብቶች የግንባታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ቶሎሳ በዳዳ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ስምምነት ከተፈራረሙ ተቋማት መካከል ከ10 በላይ የሚሆኑት በፋርማሲዪቲካል ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚፈለገውን ደረጃ እና መስፈርት ያሟላ የግንባታ ስራን በማከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ አሁን ላይ 5 ኩባንያዎች የግንባታ ስራዎችን በማጠናቀቅ ምርት የማምረት እና የሙከራ ምርቶችን በማምረት ላይ መሆናቸውን የገለጹት ስራ አስኪያጁ እነዚህ ኩባንያዎች አሁን ላይ ከ4000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ፈጥረውላቸዋል ብለዋል፡፡
የፋርማሲዪቲካል የኢንቨስትመንት ዘርፍ ከሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለየ መልኩ አስገዳጅ ደረጃዎችን ማሟላት የሚጠይቅ በመሆኑ እና የተለየ ጥንቃቄ የሚሻ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኑን የኃይል አቅርቦት ለማስፋት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በመመደብ የማስፋፊያ ስራዎች በመስራት ላይ መሆኑን አቶ ቶሎሳ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከ26 በላይ ባለሃብቶች በስራ፤በግንባታ እንዲሁም የመሬት ርክክብ ፈጽመው በተለያየ የስራ ሂደት ላይ ሲሆኑ በቀጣይም በፋርማሲዩቲካል እና በሃይቴክ ኢንቨስመንት ዘርፍ ባለሀብቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊወን ዝግጅት አድርገው ባለሀብቶችን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#kilintospecialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30