• Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 hours, 5 minutes ago
  • 7 Views

የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ስራ እዲጀምሩ ጥሪ ቀረበ

የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ስራ እዲጀምሩ ጥሪ ቀረበ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ስራ እዲጀምሩ ጥሪ  አቀረቡ፡፡ 
ዋና ስራ አስፈጻሚው በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከተገኙ የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያ ባለቤቶች ጋር በነበራቸው ውይይት ባለሀብቶቹ በድሬ ዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ሀብታቸውን እና እውቀታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ከወሰኑ ኮርፖሬሽኑ ደረጃውን የተጠበቀ መሰረተ ልማት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚያቀርብላቸው ገልጸዋል፡፡ 
በፎረሙ ኢትዮጵያ በትራንስፖርት፣ በሎጀሰቲክ እና መሰረተ-ልማት ዘርፍ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ከማብራራታቸው በተጨማሪ በኢትዮጵያ እያደጉ የመጡ ሀገራዊ እስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንቶችን እድገት ለመደገፍ የሚያስፈልጉ የትራንስፖርት እና የሎጀሰቲክ  ዘርፍ ለውጪ ቀጥተኛ አንንቨስትመንት ክፍት መደረጋቸውን አብራርተዋል፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን እንደ ተቋቋመ አንድ የመንግስት ልማት ድርጅት የውጪ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን ስራ ላይ ሲያወሉ ቆይታቸው መልካም እንዲሆን የተቻለውን እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡ 
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስታዳራቸው 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ከ200 በላይ የሚሆኑ ኩባኒያዎች በስራ ላይ የሚሚገኙ ሲሆን ኩባኒያዎቹ ከ100 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ስራ እድል መፍጠር ችለዋል፡፡ 
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#weekend 
#specialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30