• Striving for eco industrial park
logo

የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች 22ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን አከበሩ

የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች 22ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን አከበሩ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤትና በአዲስ አበባ የሚገኙ ቅርንጫፎች የስራ መሪዎችና ሰራተኞች 22ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ትናንት አክብረዋል።

በዕለቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ጃለኔ ሃሰን ሙስና ተቋማትን የሚያዳክም፤የትውልድን እድገት የሚያቆምና የማህበረሰብን እምነት የሚሸረሽር በመሆኑ ሁሉም ያገባኛል የሚል ዜጋ ሁሉ ግንዛቤ በመፍጠርና በቁርጠኝነት መታገል እንደሚጠበቅበት ጠቅሰው ኮርፖሬሽኑም ትክክለኛ አሰራርን በመተግበር ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ሃገርን ለማስረከብ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ በአግባቡ ይወጣል ብለዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የስነ_ምግባርና ጸረ_ሙስና መምሪያ ሃላፊ አቶ ጉሊድ አብዲ በበኩላቸው የሙስና ወንጀል በሃገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ሁሉም ዜጋ ግንዛቤ ወስዶ በጋራ መታገል ላይ መጠነ ሰፊ ርብርብ ማደረግ ካልተቻለ ለነገው ትውልድ የተሻለች ሃገርን ልናስተላልፍ አንችልም ብለዋል፡፡

“ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር” በሚል መሪ ቃል የተከበረው 22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን የኮርፖሬሽኑ የዋና መስሪያ ቤት፣በአዲስ አበባ የሚገኙ የቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ፣የአዲስ ኢንዱስትሪ መንደር እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የስራ መሪዎችና ሰራተኞች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በዕለቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው መልስ የተሰጠባቸው ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ያከናወኑበትን ሰነድ ርክክብም ተደርጓል።

#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#HawassaSEZ
#InvestEthiopia
#itparks
#information
#informationtechnology
#innovation
#InnovationInAction

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30