ነጻ የንግድ ቀጠናው የታለመለትን ሃገራዊ ተልዕኮ እንዲወጣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው፦ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)
የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የታለመለትን ሃገራዊ ራዕይና ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ትብብርና ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ገበተው በመስራት ላይ የሚገኙ ባለሃብቶች በተሟላ አቅም ወደ ስራ እንዲገቡ እና በተግባር እየተፈጠሩ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የሃገራችን አብዛኛው የገቢ ንግድ የሚገባው በጅቡቲ በኩል በመሆኑና ነጻ የንግድ ቀጠናው በጅቡቲ ያለውን መጨናነቅ ከመቀነስ ባለፈ ለባለሃብቶች የሚያጋጥሟቸውን የአስራር ክፍተቶች በመቀነስ የተሟላ የንግድ ስርዓት እንዲፈጥር የሚያግዝ እንዲሁም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አራት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት በነፃ ንግድ ቀጣናው በኩል ለማሳለጥ ግብ ተቀምጦ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸው ለስኬታማነቱም ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን መወጣት ያለበት መሆኑን ዶ/ር ፍሰሃ በመድረኩ ገልጸዋል ።
በመድረኩ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ሃብታቸውን ስራ ላይ የሚያወሉ ባለሃብቶች የሚያገኟቸው ጥቅሞችና ማበረታቻዎች ዙሪያ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በሌላ በኩል በነጻ የንግድ ቀጠናው ገብተው በመስራት ላይ ከሚገኙ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆኑው ሞሃን ፒኤልሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ሃሪሽ ኩታሪ የስራ ልምዳቸውንና ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነፃ የንግድ ቀጣና ሲሆን፣ ሀገሪቱን ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር ለማስተሳሰር የተቋቋመ ሲሆን ወደ ስራ ከገባ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች በቀጣናው በኩል ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሲሆን አሁን ላይ ከ45 በላይ ትልልቅ ኢንቨስተሮች ገብተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በመድረኩ ከባለሃብቶች ለተነሱ ጥያቄዎች ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፤ከብሄራዊ ባንክ፤ክጉምሩክ ኮሚሽን፤ከኢትዮጵያ ባህርና እና ሎጅስቲክስ፤ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወካዮችና የስራ ሃላፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#HawassaSEZ
#InvestEthiopia
#itparks
#information
#informationtechnology
#innovation
#InnovationInAction
#russia
#russiaembassyinaddisababa
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30