ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ከ900 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት ስራ መጀመራቸው ተገለጸ
ቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በተጠናቀቀው የፈረጆች ዓመት ከ900 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ወደ ስራ መግባታቸውን ተገለጸ፡፡
የልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አመት በርካታ ስራዎች የተሰሩበት አመት መሆኑን ጠቅሰው ከ900 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ ባለሀብቶች አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ወደ ስራ የገቡበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ ይህንን የገለጹት የፈረንጆችን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
በዓመቱ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸን የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ ለዚህ ስኬት መብቃት ደግሞ የባለሃብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንና አቶ ትንሳኤ ጠቁመው በአዲሱ አመትም ይህንን ስኬት አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የባለሃብቶች ህብረት ሰብሳቢ ሱረሽ ፒኬ በበኩላቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ለስራቸው ስኬት ከሚያደረገድ ድጋፍ በተጨማሪ አብሮነትን ለማሳየት በማሰብ ላዘጋጀው ዝግጅት እና መልካም ምኞት በዞኑ በሚገኙ ባለሃብቶችና በማህበራቸው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል አንዱ ሲሆን አሁን ላይ ከ 35 በላይ ትልልቅ ኢንቨስተሮች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ከ31 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#HawassaSEZ
#InvestEthiopia
#itparks
#information
#informationtechnology
#innovation
#InnovationInAction
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30