በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ለውጪ ገበያ ካቀረበችው ምርቶች ከግማሽ በላዩ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የተመረተ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ለውጪ ገበያ ካቀረበችው የአምራች ኢንዱስትሪ ምርቶች ውስጥ ከግማሽ በላዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ መመረታቸውን ኮርፖሬሽኑ አስታወቀ፡፡
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ኢትዮጵያ ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ 204 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶች ለውጪ ገበያ ያቀረበች ሲሆን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች አምርተው ለውጪ ገበያ ካቀረቡት ምርቶች ከ112.6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ይህም የሀገራዊ አፈጻጸሙን 55 በመቶ እንደሚሽፍን ኮርፖሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ13 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምርት ኮርፖሬሽኑ ከሚስተዳደድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች አምርተው ለሀገር ውስጥ ገበያ አቅርበዋል።ባለፉት 6 ወራት ለሀገር ውስጥ ገበያ የቀረበው የምርት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ61 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከ161 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ሲሆኑ ከ85 ሺህ በላይ የሚሆነው የስራ ዕድል የተፈጠረው ኮፖሬሽኑ በሚያስተዳራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስሪ ፓርኮች ወስጥ ነው።
በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ባለፉት 6 ወራት ብቻ 74 ድርጅቶች 4800 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ዘላቂ የሆነ ተጨማሪ የገበያ ትስስር መፍጥር የቻሉ ሲሆን በተፈጠረው የገበያ ትስስር ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸም መቻሉ ተገልጿል፡፡
#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30