• Striving for eco industrial park
logo

የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነት በዘላቂነት ለማሳደግ ችግር ፈቺ አመራር ከምንጊዜውም በላይ ያስፈልጋል፦ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

የኮርፖሬሽኑን ትርፋማነት በዘላቂነት ለማሳደግ ችግር ፈቺ አመራር ከምንጊዜውም በላይ ያስፈልጋል፦ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ትርፋማነትን ለማሳደግ ሁሉም የተቋሙ አመራር እና ሰራተኛ ከመቼውም ጊዚ በላይ ችግር ፈቺ መሆን እንዳለበት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአዳማ ከተማ በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ የኮርፖሬሽኑ የቀጣይ ስድስት ወራት የትኩረት አቅጣጫ በዘረዘሩበት የማጠቃለያ ንግግራቸው በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ያሉ ሼዶችን ማስያዝ፤የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ከድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ጋር ማስተሳሰር፤ለባለሃብቶች የተለየ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ህንጻዎችን በኪራይ ማስያዝ እና የወሰን ማስከበር ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የኮርፖሬሽኑን ውጤታማነትን ማረጋጋጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ኢትዮጵያን የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል የዲጅታላይዜሽን ስርዓትን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ተደራሽ ማድረግ፤ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጣ ያሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን መሶብ ከተሰኘው ሀገር አቀፍ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጋር ለማስተሳሰር በትኩረት እንደሚሰራም ዋና ስራ አስፈጻሚው አስምረውበታል፡፡

ከላይ የተገለጹትን ግቦች ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመለወጥ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች ከምንጊዜው በላይ ችግር ፈቺ እና ተራማጅ መሆን ይጠበቅባችዋል ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው የስራ መመሪያቸውን ቋጭተዋል፡፡



#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30