የብራዚል የቢዝነስ ልዑካን ቡድን በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ጉብኝት አደረጉ
ከ40 በላይ የየሚሆኑ የብራዚል የቢዝነስ ልዑካን ቡድን አባላት በቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
ባለሀብቶቹ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ ባደረጉት ጉብኝት፤ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉት ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ሃብታቸውን እና እውቀታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ሰፊ አማራጮች መፈጠራቸውን እንደተገነዘቡ አመላክተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የኢትዮ-ብራዚል የቢዝነስ ፎረም ላይ ከተካፈሉ በኋላ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ ያለውን የኢንቨስትመንት ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ።
በጉብኝቱ ወቅት ለልዑካን ቡድኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ ስለሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ስለሚገኙ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች እና መንግስት ለዘርፉ ባለሀብቶች ስለሚያቀርባቸው ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ልዑል ሰገድ ታደሰ ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት ባከናወነችው ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ስራ፣ ለኢንቨስትመንት ተገማችና ማራኪ የሆነ ምህዳር መፍጠር መቻሏን ገልጸው የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ የማምረት አቅም እና ለኢንቨስትመንት የተመቻቸ ዝግጁነትን በመገንዘብ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮ-ብራዚል የቢዝነስ ፎረም በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ያለመ ሲሆን በፎረሙ ማጠቃለያ ላይ የሁለቱም ሃገራት የኢኮኖሚ ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ የመግባቢያ ስምምነቶች መፈረማቸው ይታወሳል ።
#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30