የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጊዜውን የዋጀ አመራር ለመስጠት የሚረዳ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተቋሙን በተለዋዋጭ ዓለማዊ ሁኔታ ውስጥ ውጤታማ በሆነ አግባብ ለመምራት የሚረዳ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ፡፡
ስልጠናው ተለዋዋጭ በሆነ ዓለማዊ ሁኔታ ውስጥ መሪዎች እንዴት ጊዜውን የዋጀ አመራር መስጠት ይችላሉ በሚለው ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ የተደራጀ መሆኑን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጃለኔ ሀሰን ተሳታፊዎች ስልጠናውን በአግባቡ ከተከታተሉ ብዙ ቁምነገር እንደሚገበዩ ጠቁመዋል፡፡
ፈጠራ በታከለበት እና ዓለማዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ውጤት ተኮር ስልጠና ለመስጠት የሚረዱ ስልቶችን ለመተግበር ስልጠናው እንደሚያግዝ የገለጹት የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን ስልጠናው ሰልጣኞችን የሚያነቃቃ፣ አስተሳሰባቸውን የሚፈትን እና በሂደት ውስጥ አዲስ ሀሳብ እንዲገበዩ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ፈጠራ የታከለበት ፣ጊዜውን የዋጀ እና ውጤታማ አመራር ለመስጠት የሚረዱ ተግባራዊ ስልቶች በተግባር የሚከወንበት አውድ ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል፡፡
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በኢትዮጵያ በማማከር እና በማሰልጠን ለግማሽ ምዕተ ዓመት ገደማ በሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ደማቅ አሻራ ማሳረፍ የቻለ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ ከልማታዊ መንግስት እሳቤ ወደ ኢንተርፐርነሪያል መንግስት እሳቤ ያደረገቸውን ሽግግር በመደገፍ ላይ ያለ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30