• Striving for eco industrial park
logo

ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

 

‘በኮርፖሬት ኢንተርፐርነርሺፕ’ እና አስቻይ ስነምህዳር ግንባታ አስፈላጊነት ላይ በማተኮር ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል፡፡

 

በአቅም ማጎልበቻ ስልጠናው የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተለዋዋጭ በሆነ ዓለማዊ ሁኔታ ውስጥ  ጊዜው የሚጠይቀውን አመራር መስጠት እንዲችሉ በማድረግ የኮርፖሬሽኑን ተወዳዳሪነት እና ትርፋማነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

 

የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጃለኔ ሀሰን ስልጠናው ኮርፖሬሽኑ ላለበት የዕድገት ደረጃ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባባር ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል፡፡

 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን የኮርፖሬሽኑን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ታልሞ ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመው ስልጠናውን እውን ለማድረግ የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ላደረገው ትብብር በኮርፖሬሽኑ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

ለአራት ተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱ በተሰጠው ስልጠና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣  እንዲሁም የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል፡፡