• Striving for eco industrial park
logo

ኮርፖሬሽኑ በሃገር ውስጥ የተገጣጠሙ የኤሌክትሪክ መኪኖች ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ተረከበ

ኮርፖሬሽኑ በሃገር ውስጥ የተገጣጠሙ የኤሌክትሪክ መኪኖች ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ተረከበ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገጣጠሙ 26 የኤሌክትሪክ መኪኖች ተረክቧል፡፡

የኤሌክትሪክ መኪኖቹን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ መስራችና ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) አስረክበዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት በኤሌትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን መግዛቱ ኮርፖሬሽኑ አካባቢን ከብክለት ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት ጥሩ ማሳያ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች ግዥ ሲፈጽም ያሁኑ የመጀመሪያው አለመሆኑን ያስታውሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዛሬው እለት በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ተገጣጥመው ኮርፖሬሽኑ የተረከባቸውን መኪኖችን ጨምሮ ከ50 በላይ በኤሌትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን እንዳሉት አመላክተዋል፡፡

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ መኪኖቹን በአጭር ጊዜ ገጣጥሞ በማስረከቡ በኮርፖሬሽኑ ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ ባለሀብቱ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሀብት እና እውቀታቸውን ስራ ላይ እንዲያውሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ባለቤትና መስራች አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ የሃገርን እድገት ለማፋጠንና ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ለማስፋፋት እየሰራቸው ያለውን ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸው በዛሬው እለት ርክክብ የተደረገባቸው መኪኖች የተሻለ አቅምና ጉልበት ያላቸው እንዲሁም በቂ መለዋወጫና የጥገና ማዕከል ያላቸው መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም ከኮርፖሬሽኑ ተባብረው ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ዋና መስሪያ ቤት የሚጠቀማቸው መኪኖች ቁጥር ውስጥ እስካሁን የኤሌክትሪክ መኪኖች 30 በመቶውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን በሂደት በኤሌትሪክ በሚሰሩ ተሸከርካሪዎች ለመተካት አበክሮ በመስራት ላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ወደ ስራ ያስገባቸው የኤሌቲሪክ መኪኖች ለሰራተኞች የሚሰጡ የሰርቪስ አገልግሎት ምቾት እንዲኖረው ከማስቻላቸው በላይ ተቋሙ ለመኪና ኪራይ እና ለነዳጅ በዓመት የሚያወጣውን ወጪ ትርጉም ባለው መልኩ አንደሚቀንስ ይታመናል፡፡


#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
#BKG
#belaynehkindiegroup

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30