• Striving for eco industrial park
logo

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን የምርታማነት አቅም ለማሳደግ የሚያስችል እመርታዊ የአሰራር ምኅዳር መፍጠሩ ተገለጸ

ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን የምርታማነት አቅም ለማሳደግ የሚያስችል እመርታዊ የአሰራር ምኅዳር መፍጠሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፤ እመርታዊ የፖሊሲና የአሰራር ምኅዳር በመፍጠር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያላቸውን ድርሻ እያሳደገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ትብብር "ኢትዮጵያ - አዲሲቷ የኢንቨስትመንት መዳረሻ" በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ነው ።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፐሬሽንና ፓርክ አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍጹም ከተማ ባደረጉት ንግግር፤ ሀገር በቀሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ን የምርታማነት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል።

የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የፈጠረው እመርታዊ የፖሊሲ እና የአሰራር ምኅዳር፣ ፓርኮቹ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ይበልጥ እንዲያጎለብቱ እያስቻላቸው መሆኑንም ስራ አስፈጻሚው አብራርተዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ፤ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በረከት ፍስሃፅዮን፣ የጤና ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ፤የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን፣ የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሞቱማ ተመስገን እንዲሁም የኢዜአ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ ፤ የፌደራል እና ክልል የኢንቨስትመንት ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ባለሀብቶች ተሳትፈውበታል፡፡

#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
#EthiopianInvestment

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30