• Striving for eco industrial park
logo

ቻይና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያላትን ኢንቨስትመንት በእጥፍ ለማሳደግ እንደምትሰራ ገለጸች

ቻይና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያላትን ኢንቨስትመንት በእጥፍ ለማሳደግ እንደምትሰራ ገለጸች

በኢትዮጵያ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ቼን ሃይ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የቻይናን ኢንቨስትመንት በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በእጥፍ ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፉ ገለጹ።

አምባሳደሩ ይህንን የገለጹት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ከተማ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።

በውይይቱም በኢትዮጵያ የቻይናን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት፣ የሁለቱን ተቋማት ትብብር ለማጠናከርና የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ ምክክር ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት አቶ ፍጹም ከተማ ኮርፖሬሽኑ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያስመዘገበውን አፈጻጸም፣ ተቋማዊ ተልዕኮውንና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ልማት ያለውን እየሰፋ የመጣ ሚና ለአምባሳደሩ ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችንና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እያስተዳደረ ሲሆን፣ ከ300 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶችን በማስተናገድ ከ100 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎችን መፍጠሩን አስረድተዋል።

ከኮርፖሬሽኑ በሚተዳደሩ ተቋማት ውስጥ ከሚገኙ ባለሀብቶች መካከል 200 የሚጠጉት ማምረት የጀመሩ ሲሆን፣ 43ቱ የቻይና ኩባንያዎች ናቸው። ይህም የቻይና ባለሀብቶች በኮርፖሬሽኑ የኢንዱስትሪ ተቋማት ውስጥ ካሉ ባለሀብቶች ውስጥ ከአንድ አራተኛ ገደማውን የሚይዙ ሲሆን፣ ቻይናንም በውጭ ኢንቨስትመንት ቀዳሚ ምንጭ አገር እንደሚያደርጋት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።

አምባሳደር ቼን ሃይ ይህንን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ አዳዲስ የቻይና የንግድ ልዑካን ቡድኖችን ከኮርፖሬሽኑ ጋር ለማገናኘት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ወሳኝ ምሰሶ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ቻይና በልማት ጉዞዋ ካሳለፈችው ተሞክሮ በመነሳት ጠንካራ የኢንዱስትሪ መሠረት መገንባት ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል። የኢንዱስትሪ ልማት የከተሞችን መስፋፋት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራንና አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን የሚያፋጥን መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የቻይናን ኢንቨስትመንት ለመሳብ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የሚገጥማት ውድድር እየጨመረ መምጣቱን አምባሳደሩ አስጠንቅቀዋል። በተለይም የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ወጪዎች፣ የግብር ሥርዓት፣ የኤሌክትሪክ ዋጋ፣ የሠራተኛ ግንኙነቶች እንዲሁም የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ፖሊሲዎች ተገማችነት የቻይና ባለሀብቶች ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም አንጎላ፣ ኡጋንዳ፣ ናሚቢያ፣ ሩዋንዳና ዛምቢያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከቻይና ጋር ያላቸውን ትብብር እያጠናከሩ መምጣታቸውንና የቻይና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በፉክክር ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ሥርዓቷን እንድታጠናክርና የአገሪቱን ተወዳዳሪነት የሚገድቡ ችግሮችን እንድትፈታ ያበረታቱት አምባሳደሩ፣ የተረጋጋና ተገማች የንግድ አካባቢ መፍጠር የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለማቆየት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በምላሹም የአይፒዲሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮርፖሬሽኑ በሚተዳደራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የቻይና ባለሀብቶች ድጋፍ ለማድረግና የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ለማመቻቸት በተቋሙ የሕግ ማዕቀፍ መሠረት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ከኢንቨስትመንት ማስፋፋት ባሻገር የተቋማትን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችሉ ዕድሎችም በውይይቱ ተነስተዋል። አቶ ፍጹም ከተማ ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች በውጭ አገር የሥልጠና ዕድሎችን ለማመቻቸት፣ በቻይና ኩባንያዎች ላይ ያተኮረ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ ሥራን ለማጠናከርና የኮርፖሬሽኑን የተቋማዊ ለውጥ ሥራ ለመደገፍ የኤምባሲውን እገዛ ጠይቀዋል።

አምባሳደሩም ጥያቄዎቹን በአዎንታዊ መንፈስ በመቀበል፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማመቻቸት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም ኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ መልክ የማደስ ሥራ ላይ ሙያ ድጋፍ ሊያደርጉ ከሚችሉ የቻይና ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር እንደሚያግዙ አረጋግጠዋል።

በውይይቱ የፖሊሲ ቀጣይነትና ከቻይና የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ዘላቂ ግንኙነት መፍጠር ያላቸው ፋይዳም ተነስቷል። በተለይም ከግብር፣ ከኢሚግሬሽን ሥርዓቶች፣ ከኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችና ከአጠቃላይ የንግድ አካባቢ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በኢትዮጵያ በሚንቀሳቀሱ የቻይና ኩባንያዎች መካከል ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል።

አምባሳደሩም የባለሀብቶችን ስጋቶች ለመፍታትና የንግድ እምነትን ለማጠናከር ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ተቋማት ጋር ለመሥራት ኤምባሲው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሯን ለማፋጠንና የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ የውስጥ ምርት (GDP) ያለውን ድርሻ ለማሳደግ የምትከተለው የረጅም ጊዜ የልማት ስትራቴጂ በውይይቱ ተካቷል። ሁለቱም ወገኖች ብሔራዊ የልማት ዓላማዎችን በኢንዱስትሪ ማስፋፋት፣ በኢንቨስትመንትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት መቀየር ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ውይይቱ ሁለቱም ወገኖች የተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር፣ የቻይናን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋትና የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ሂደት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ ተጠናቋል።

ይህ ውይይት ኮርፖሬሽኑ አዲሱ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ ከጸደቀ በኋላ ሰፋ ያለ ተቋማዊ ሚና ለመሸጋገር በሚዘጋጅበት ወሳኝ ወቅት መካሄዱ ልዩ ፋይዳ አለው። ተቋማዊ መልክ የማደስ ሥራ ላይ ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያን ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች በማልማትና በማስተዳደር የበለጠ ሰፊ ሚና እንዲኖረው የሚያስችለው ነው።

China to Stregthen Chinese Investment in Ethiopia’s Industrial Parks

The Ambassador of the People’s Republic of China to Ethiopia, Chen Hai, has promised to support efforts to double Chinese investment in industrial parks and Special Economic Zones (SEZs) administered by the Industrial Parks Development Corporation (IPDC) within the next two years.

The announcement was made during a meeting between Ambassador Chen Hai and IPDC Chief Executive Officer, Fitsum Ketema.

The leaders discussed on how to expand Chinese investment in Ethiopia, strengthening institutional cooperation and enhancing the competitiveness of the country’s industrial investment.

During the meeting, Fitsum briefed the Ambassador on IPDC’s investment performance, institutional mandate and expanding role in Ethiopia’s industrial development. He noted that the Corporation currently administers 14 Special Economic Zones and industrial parks, hosting more than 300 local and international investors and generating over 100,000 employment opportunities.

Out of the total investors operating in IPDC-administered facilities, approximately 200 are actively engaged in manufacturing, including 43 Chinese companies. Chinese investors account for roughly one-quarter of active investors, making China the leading source country of foreign investment in the Corporation’s industrial facilities noted Fitsum.

Ambassador Chen expressed his commitment to strengthening this investment presence, promising to facilitate connections between incoming Chinese business delegations with IPDC.

He underscored industrialization as a critical driver of Ethiopia’s economic transformation, drawing on China’s own development experience to emphasize the importance of building a strong industrial base. He noted that industrial development would also accelerate urbanization, employment creation and broader economic growth.

However, the Ambassador cautioned that Ethiopia faces increasing competition from other African countries seeking to attract Chinese manufacturing investment. He identified transportation and logistics costs, taxation, electricity prices, labour relations and the predictability of investment incentives and policies as important considerations shaping Chinese investors’ decisions.

He also an increasing cooperation from other African countries like Angola, Uganda, Namibia, Rwanda and Zambia among countries competing for Chinese investment.
He encouraged Ethiopia to strengthen its investment incentive framework and address challenges affecting the country’s competitiveness, noting that a more predictable business environment would be essential to attracting and retaining foreign investment.

In response, the IPDC CEO reaffirmed the Corporation’s commitment to supporting Chinese investors and facilitating their operations within its industrial parks and SEZs, in accordance with its institutional mandate and the applicable legal framework.

The two sides also discussed opportunities to deepen institutional cooperation beyond investment attraction. Fitsum requested the Embassy’s support in facilitating overseas training opportunities for IPDC staffs, strengthening investment promotion activities targeting Chinese companies and supporting the corporations rebranding effort.

The Ambassador welcomed the requests and expressed readiness to facilitate the necessary connections, particularly with Chinese companies that could provide professional support for IPDC’s institutional rebranding initiative.

The discussions also highlighted the importance of policy consistency and sustained engagement with the Chinese business community in Ethiopia. It was noted that issues relating to taxation, immigration procedures, investment policies and the broader business climate remain important areas of discussion among Chinese businesses operating in the country.

The ambassador reaffirmed the Embassy’s willingness to engage with relevant Ethiopian institutions to help address investors’ concerns and strengthen business confidence.

The meeting further addressed Ethiopia’s long-term development strategy and the need to accelerate structural transformation by strengthening the industrial sector’s contribution to GDP. Both sides emphasized the importance of translating national development ambitions into tangible economic outcomes through industrial expansion, investment and job creation.

The meeting concluded with both parties reaffirming their commitment to strengthening institutional cooperation, expanding Chinese investment and advancing Ethiopia’s industrialization agenda.

The engagement comes at a significant time for IPDC as the Corporation prepares to transition into a broader institutional role following the ratification of the new Special Economic Zone Proclamation.

The expanded mandate is expected to be reflected in its planned institutional rebranding effort, positioning the institution to play a wider role in the development and administration of Ethiopia’s Special Economic Zones.