• Striving for eco industrial park
logo
  • by ipdcadmin
  • 0Comments
  • 10 hours, 50 minutes ago
  • 30 Views

ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው ሶስት የቻይና ኩባንያዎችን በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የግንባታ ስራ አስጀመሩ

ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው ሶስት የቻይና ኩባንያዎችን በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የግንባታ ስራ አስጀመሩ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የፓርክ አስተዳደር እና ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ከተማ የሶስት የቻይና ኩባንያዎችን በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የግንባታ ስራ አስጀመሩ፡፡

ፕሮጀክቱ በሶስት ነጥብ ሰባት ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ዘጠኝ የተለያየ መጠን ያላቸው የፋብሪካ ሼዶች እና አራት የቢሮ ህንጻዎችን የሚያካትቱ መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው በኮስሞቲክስ እና በሜዲካል ፓኬጅንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባኒያዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ኩባንያዎቹን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራራች ተደጋጋሚ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፍጹም ከተማ ጥረቱ ፍሬ አፍርቶ ኩባኒያዎቹ የግንባታ ስራ ማስጀመራቸው መልካም መሆኑን አውስተው ባለሀብቶቹ ግንባታውን በአጠረ ጊዜ አከናውነው ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የኩባንያዎቹ ባለቤቶች የግንባታ ስራውን ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያውያን የስራ እድል ከመፍጠር በተጨማሪ ምርቶቻቻውን ለሀገር ውስጥ ገቢያ እና ለውጪ ገበያ በማቅብ ሀገሪቱ በዘርፍ የሚመረቱ ምርቶችን ከውጪ ሀገር ለማስገባት የምታወጣውን የውጪ ምንዛሬ ከማስቀረት በተጨማሪ የውጪ ምንዛሬ ገቢ ማስገባት እደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ዲኤፍ ኮሰሞቲክስ፣ ካልካሊ እና ሮድማፕ የተባሉ ኩባኒያዎች ለግንባታ ስራው አስር ሚሊንየን ዶላር ገደማ ስራ ላይ እደሚያውሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Three Chinese Companies Begin Factory Construction at Kilinto Special Economic Zone

Three Chinese companies have commenced factory construction at the Kilinto Special Economic Zone, with the companies expected to invest approximately USD 10 million in the project.

Fitsum Ketema, Deputy Chief Executive Officer for Park Administration and Operations at the Industrial Parks Development Corporation (IPDC), officially launched the construction work for the three companies.

The project will cover 3.7 hectares of land and comprise nine factory sheds of varying sizes and four office buildings. According to Fitsum Ketema, the companies operate in the cosmetics and medical packaging industries.

Recalling the repeated efforts made by the corporation’s senior leadership to attract the companies to Ethiopia, Fitsum expressed satisfaction that these efforts had yielded results and that construction had commenced. He also assured the investors that the corporation would provide the necessary support to help them complete construction within a short period and begin operations as soon as possible.

The owners of the companies, meanwhile, indicated that they plan to complete the construction work in less than one year. Once operational, the factories are expected to create employment opportunities for Ethiopians and contribute to the national economy by supplying products to both domestic and international markets.

In particular, the companies are expected to help reduce foreign currency expenditure by substituting imported products with locally manufactured alternatives. They are also anticipated to generate foreign currency earnings through exports.

The three companies—DF Cosmetics, Calcali, and Roadmap—are expected to invest a combined total of approximately USD 10 million in the project.