• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 1 week ago
  • 128 Views

ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን

"ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ለመቀየር የሚከናወኑ ተግባራት ባጠረ ግዜ ውጤታማ እንዲሆኑ ይሰራል" ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የነፃ ንግድ ቀጠናዎች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በልዩ የኢኮኖሚ ዞን አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ሰጥቷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ  መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ፍስሃ ይታገሱ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለመቀየር የሚከናወኑ ተግባራት ባጠረ ግዜ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚሰራ ገልፀው ሁሉም በኃላፊነትና በባለቤትነት ስሜት እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በተጨማሪም የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጁን ለመተግበር እየተማሩ መስራት ፤ እየሰሩ መማርን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁላችንም በኃላፊነትና በፍጥነት ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የመምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል ።

የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ፤ ቀልጣፋና አመቺ የኢንቨስትመንትና የንግድ ሁኔታ ለመፍጠር ፤ መሰረተ ልማቶችን በተሻለ መልኩ ለማሟላት ፤ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን ፤ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር እና የአካባቢ ተፅዕኖን ለመቀነስ በአዋጅ ቁጥር 1322/2016 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ይታወሳል።

"Efforts will be aggressively done to transform industrial parks into special economic zones in the shortest possible time" Dr.

Industrial Parks Development Corporation's
Free Trade Zones Coordinating Office  has given awareness training on the implementation of the Special Economic Zone today.

Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu, who delivered a message at the awareness forum, stated that the efforts to transform the industrial parks into a special economic zone will be done effectively in short period of time and urged everyone to act with a sense of responsibility and ownership.

The CEO also stated that since the new special economic zone proclamation requires learning while doing, we all have to work responsibly and quickly for its implementation.

IPDC Management members, Managers of industrial parks as well as heads of departments participated in the awareness training.

Proclamation of Special Economic Zone was approved by the House of Representatives with Proclamation No. 1322/2016 to increase the country's economy, to create an efficient and favorable investment and business environment, to better complement the infrastructure, to accelerate technology transfer, to create job opportunities and reduce environmental impact.

#SpecialEconomicZone