• Striving for eco industrial park
logo
  • by ipdcadmin
  • 0Comments
  • 11 hours, 36 minutes ago
  • 21 Views

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በ"ተስፋን እንትከል" ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ተሳተፉ

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በ"ተስፋን እንትከል" ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ተሳተፉ

 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ንቅናቄ በመቀላቀል በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ችግኞችን ተክለዋል።

 

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፣ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 14 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ560 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።

 

ዶ/ር ፍሰሃ እንዳሉት፣ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ሰባት ዓመታት በ14ቱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች በየዓመቱ በአማካይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የ78 በመቶ የመጽደቅ ምጣኔ ማስመዝገቡን ጠቁመዋል።

 

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በተካሄደው የሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት፣ የመምሪያ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በንቃት ተሳትፈዋል።

 

ኮርፖሬሽኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በቀጣይነት በማጠናከር የአካባቢ ጥበቃን፣ የአረንጓዴ ልማትን እና የዘላቂ ኢኮኖሚ ግንባታን ለማጎልበት ያለውን አስተዋፅኦ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተገልጿል።