የናሚቢያ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ልምድ ለመገንዘብ የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኘ
በናሚቢያ ሪፐብሊክ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስትር ጄምስ ሳንክዋሳ የተመራው ከፍተኛ የመንግሥት ልዑካን ቡድን አባላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ልምድ ለመገንዘብ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኙ።
የልዑካን ቡድኑን አባላት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጃለኔ ሐሰን ተቀብለዋቸዋል። በዚህም የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ስለ ኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ገለጻ አድርገዋል።
የናሚቢያ ሪፐብሊክ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስትር ጄምስ ሳንክዋሳ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው፣ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ ያገኙት ልምድ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከርና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
ለልዑካን ቡድኑ አባላት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለው የሥራ እንቅስቃሴ፣ ዞኖቹ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያላቸው አስተዋጽኦ፣ በዞኖቹ የሚገኙ ባለሀብቶች የሥራ እንቅስቃሴና የተሰጡ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
ልዑካን ቡድኑ በተጨማሪም በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚገኘውን የሽንትስ ኩባንያ የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል።
የናሚቢያ ልዑካን ቡድን አባለት ላለፉት ስስት ቀናት ከኢትዮጵያን ልምድ ለመቅሰም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጨማሪ የተለያዩ የሀገሪቱን ተቋማት በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
Namibian Delegation Visits Ethiopia’s Special Economic Zones to Learn from its Industrial Development Experience
A high-level Namibian government delegation, led by Namibia’s Minister of Urban and Rural Development, James Sankwasa, has visited Ethiopia’s Bole Lemi and Kilinto Special Economic Zones to gain insights into the country’s industrial development experience.
The delegation was received by Mrs. Jalene Hassan, Deputy CEO of the Investment Promotion and Marketing Division of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC). She welcomed the delegation and briefed its members on the corporation’s activities and its role in developing and managing industrial parks and special economic zones.
During the visit, the delegation received briefings on the operations of the special economic zones, their contribution to Ethiopia’s economy, the activities of investors operating within the zones, and the investment incentives available to businesses.
Minister Sankwasa expressed his appreciation for the reception and said the experience gained during the visit would help strengthen relations between Namibia and Ethiopia.
The delegation also visited Shints, a company operating in the Bole Lemi Special Economic Zone, where members observed its operations and gained firsthand insights into industrial activities within the zone.
The visit forms part of a broader four-day experience-sharing program, during which the Namibian delegation has visited various Ethiopian institutions, in addition to engaging with the Industrial Parks Development Corporation, to learn from Ethiopia’s industrial development experience.