በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው የተለያዩ የእንግሊዝ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ልዑካን የቂሊንጦ እና የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን የጎበኙ ሲሆን፤ በቆይታቸውም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በኢንቨስትመንት ሁኔታዎች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በቻይናው ግዙፍ የፋርማሲዩቲካል ኩባንያ ሂውማንዌል ሄልዝኬር ግሩፕ ሰብሳቢ ደንግ ዌይዶንግ የተመራና 17 ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሥራ ጉብኝት አደረገ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የታቀደላቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲወጡና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ባለሀብቶችን ለማፍራት የፋይናንስ ተቋማት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፤ እመርታዊ የፖሊሲና የአሰራር ምኅዳር በመፍጠር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያላቸውን ድርሻ እያሳደገ መሆኑ ተገልጿል፡፡