ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት 266.9 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ገቢ መገኘቱን ገለጸ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች ተመርተው ወደ ውጭ አገራት ከተላኩ ምርቶች 266.9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በ2018 በጀት ዓመት መገኘቱን አስታውቋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ ተቋሙ ከተቋቋመ ወዲህ የተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የወጪ ንግድ አፈጻጸም ኮርፖሬሽኑ ካዘጋጀው የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አንጻር ሲታይ፣ የተያዙ ግቦችን በታቀደው ጊዜ ወይም ከታቀደው በፊት ማሳካት እንደሚቻል ያሳየ አበረታች ውጤት ነው ብለዋል።
ለዚህ ስኬት ዋነኛ ምክንያት በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ባለሀብቶችና አምራች ኩባንያዎች የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍና የቅርብ ክትትል ማጠናከር መቻሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኮርፖሬሽኑ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምን በሀዋሳ ከተማ በመገምገም ላይ ይገኛሉ።